አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. የተለያዩ መኖሪያ ቤቶችን መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 626/2001 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሀራጅ ሽያጭ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ/ዋ ስም |
የንብረት አስያዥ /የባለ ንብረቱ ስም |
የተበደሩበት ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ / የንብረቱ ዓይነት |
የንብረቱ መገለጫ |
መነሻ ዋጋ ብር |
ሐራጁ የሚካሄድበት |
|
|
ቀን |
ሰዓት |
|||||||
|
1. |
አገስ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ /ማ
|
ወ/ሮ ገነት ፍሰሐ አሰፋ |
አዲሱ ገበያ |
ቢሾፍቱ ከተማ ዱከም ክፍለ ከተማ ጠዴቻ ወረዳ የቤት ቁጥር አዲስ |
የቦታው ስፋት 202 ካ.ሜ የቤት ዓይነት የመኖሪያ |
3,273,556.25 |
ሰኔ 17 /2018 ዓ.ም. |
4፡00-5፡00 |
|
2. |
ጂቱ የእንስሳት መኖ ማምረቻ ኃ/የተ/ የግል ማህበር |
ወ/ሮ ወ/ሪት ማርታስፒሮስ ዴላፖርታስ |
ዱከም |
ቢሾፍቱ ከተማ ዲባዩ ክፍለ ከተማ ሆራ ወረዳ የቤት ቁጥር አዲስ |
የቦታው ስፋት 204.47 ካ.ሜ የቤት ዓይነት የመኖሪያ |
4,908,727.25 |
ሰኔ 17 /2018 ዓ.ም. |
5፡00-6፡00 |
|
3. |
ወ/ሮ ጀዋራ ሰብስብ እና ወ /ሮ ዝናሽ ብርሃኑ |
በቀድሞ በአቶ ወ/ሮ ጃዋራ ሰብስብ ስም በአሁኑ በአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ስም |
ኮልፌ |
ሰንዳፋ በኬ ከተማ ቀበሌ 01 በተለምዶ ዶሮ እርባታ አካባቢ |
የማጠናቀቂያ ሥራ የሚቀረው የቦታው ስፋት 200 ካ.ሜ የቤቱ ዓይነት የመኖሪያ |
2,064,768.79 |
ሰኔ 18 /2018 ዓ.ም. |
3፡00-4፡00 |
|
4. |
ወ/ሮ ዝናሽ ስሜነህ እና ዝናሽ ጸጋዬ |
በቀድሞ አቶ መስፍን አሰፋ በአሁኑ በአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ስም |
ካራቆሬ |
በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ |
የቦታው ስፋት 200 ካ.ሜ የቤቱ ዓይነት የመኖሪያ |
2,664,757.00 |
ሰኔ 18 /2018 ዓ.ም. |
4፡00-5፡00 |
|
5 |
አቶ ከማል ላሎ |
በቀድሞ አቶ ከማል ላሎ በአሁኑ በአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ስም |
ዳርጌ |
ስልክ አምባ ከተማ |
የቦታው ስፋት 121 ካ.ሜ የቤቱ ዓይነት የመኖሪያ |
200,000.00 |
ሰኔ 18 /2018 ዓ.ም. |
5፡00-6፡00 |
|
6 |
አቶ ሞገስ ተሾመ |
በቀድሞ አቶ ሞገስ ተሾመ በአሁኑ በአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ስም |
ዳርጌ |
ዳርጌ ከተማ |
የቦታው ስፋት 210 ካ.ሜ የቤቱ ዓይነት የመኖሪያ |
150,000.00 |
ሰኔ 18 /2018 ዓ.ም. |
7፡00-8፡00 |
ማሳሰቢያ
- የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25 %በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በኩባንያው ስም አሰርቶ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን አንስቶ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት ቀሪውን ክፍያ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን ባይረከብ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ በንብረቱ ላይ በድጋሚ ጨረታ ይወጣል።
- የንብረቱ ስመ ሀብት ወደ ገዥ እንዲዞር ኩባንያው ሰነዶችን ያስረክባል፤ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ሀራጁ የሚካሄድበት ቦታ፡- ተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱት መኖሪያ ቤቶች ዱከም ከተማ በድርጅቱ ዱከም ቅርንጫፍ እና ከተራ ቁ. 3 – 6 አጋርማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ዳማ ሃውስ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
- ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች መጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከሰኔ 10 – 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቤቶቹ በሚገኙበት ከተማ እና ወረዳ በአካል በመገኘት ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላል።
- የስም ማዛወሪያን ጨምሮ ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ማንኛውንም ክፍያ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል።
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ተወካዮች እና የንብረቱ ባለቤቶች ብቻ ናቸው።
- ጨረታን የሚመለከቱ ደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከላይ ከተራ ቁጥር 3 – 6 የተጠቀሱት በድርድር ሃራጅ ሽያጭ የሚስተናገዱ ሲሆን፤ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰው ቤት በመደበኛ የሃራጅ ሽያጭ የሚስተናገድ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ዋና መሥሪያ ቤት ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ዳማ ሀውስ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305፣ 302፣ 309፣ 310 ዘወትር በሥራ ሰዓት በግምባር ቀርቦ መጠየቅ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011-5-57 95 89 (የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ)፣ 011-5-57 71 89 (ህግ አገልግሎት)፤ 011-2-77 05 67 (ኮልፌ ቅርንጫፍ)፤ 011-3-69 30 41 (ካራቆሬ ቅርንጫፍ)፤ 011 -1-546109 (አዲሱ ገበያ)፤ 011 4718697 (ዱከም ቅርንጫፍ) እንዲሁም 011-3-58 03 97 (ዳርጌ ቅርንጫፍ) በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-25 14:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Aggar Micro Finance Share Company(AMFSC)
- Buyer TIN: 0002778461
- Bid bond: 25%
- Published: May 24, 2026
- Posted at: 2026-05-25T12:43:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.