መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የሰነድ ቁጥር 124

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ቁሳቁሶቹም፡-

1. የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች እና ፋይሊንግ ካቢኔቶች፣

2. ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ቴሌቪዥን፣ ዩ.ፒ.ኤስ ላፕ ቶፕ፣ ቶነር፣ውሃ ማጣሪያዎች፣ ወዘተ)፣

3. የተነቃቀሉ ጣውላዎች እና አሮጌ ጠረጴዛዎች

4. ጋዜጣ፣ ካርቶን፣ ወረቀት እና የውሃ መያዣ ባዶ ሃይላንድ

5. ያገለገሉ የመጸዳጃ ቤት ሣህኖች (ሲንኮች)፣ ቦይለሮች፣ የአምፖል ማቀፊያና ማብሪያና ማጥፊያዎች

6. በብረት የተሠሩ ቋሚ የመብራት ምሰሶዎች (ፖል)

7. አሮጌ ጎማዎች ናቸው።

በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 30-79-64-13 ወይንም 09 75- 26-41-59 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-05 11:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mekedonia Charity Association
  • Buyer TIN: 0027054421
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር )
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T08:05:21.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders