በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም ለ2019 በጀት ዓመት በመንግሥት ከሚበጀትልን መደበኛ በጀት ላይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች ምግብ አግልግሎት ላይ የሚውል የተለያየ ምግብ እህልና ማጣፈጫዎች እና ምግብ ማብስያ ማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ በማውጣት መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም ለ2019 በጀት ዓመት በመንግሥት ከሚበጀትልን መደበኛ በጀት ላይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች ምግብ አግልግሎት ላይ የሚውል የተለያየ ምግብ እህል እና ምግብ ማብስያ ማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ በማውጣት መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፡-

ሎት አንድ (1) የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል እና ማጣፈጫዎች

2. ሎት ሁለት (2) ለምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት በዚህ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመጫረቻ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

ለሎት አንድ (1)- የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል እና ማጣፈጫ ጨረታ 15,000.00 CPO. 2ኛ. ለሎት (2) በማሸግ ለምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት 5,000 CPO ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ሠነድን ከጨረታ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ

2. የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማቅረብ የሚችል፤

3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin number) ማቅረብ የሚችል፤

4. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

5.ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

6. ከክፍያው 3% ተቀናሽ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ

7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታውን ተወዳድሮ ሲያሸንፍ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዥ /CPO/ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤

8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሚዛን ማረሚያ ተቋማት በመቅረብ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሁለት ፖስታ በሰም በታሸገ በኤንቨሎፕ በማድረግ በዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

9. ከሎት አንድ ላይ የምትሳተፉ ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለሚጫረቱበት ጨረታ ናሙና ይዘው (አያይዘው) ማቅረብ አለባቸው።

10. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን 14/09/2018 ዓ/ም እስከ 14/10/2018 ዓ/ም ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በቀን 15/10/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚዛን ማረሚያ ተቋም የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በመጀመሪያው የሥራ ቀን ወይም ሰኞ የሚከፈት ይሆናል።

11. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀበት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ተቋሙ በሚያዘጋጀው ውል በመግባት ያሸነፈውን ጨረታ እስከ ተቋም ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግደታ አለበት።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  • ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ከቀን 14/9/2018 እስከ 14/10/2018 ዓ.ም ጨረታው የሚከፈተው በቀን 15/10/2018 ዓ.ም
  • ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ በሚሳተፉበት ወቅት ከላይ በቀረበው መስፈርት መሰረት የጨረታ ማስያዢያ/ C.PO ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት እለት በሰዓቱ ባይገኙም በሌሉበት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
  • አድራሻ፡- ሚዛን ማረሚያ ተቋም

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-22 14:30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Bench Sheko Zone Mizan Correctional Facility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T08:57:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders