የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ብ/ግ/ጨ/SSGI/01/2018

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዢ ሲመጡ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 1-15 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

ተቁ

የሚፈፀመው ሽያጭ

መግለጫ

1

ኤሌክትሮኒክስና የቢሮ መገልገያዎች፣ የመኪና ጎማና ባትሪ

ሎት 1

2

አሮጌ የቅየሳና አጋዥ መሳሪያዎች

ሎት 2

3. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት በኢንስቲትዩቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።

4. የጨረታ መክፈቻ ቀን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው መጀመሪያ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን ይሆናል።

5. ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ ለሚጫረቱባቸው እቃዎች የመነሻ ዋጋ አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደ አስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጎን በሚገኘው የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ኮርስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-15 ገንዘብ ቤት ነው።

የስልክ ቁጥር፡- 011-872-0286

በኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው መጀመሪያ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-04 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው መጀመሪያ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Space Science and Geospatial Institute
  • Buyer address: 6 ኪሎ ምስካህ ህዙናን መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ፊትለፊት
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T09:51:23.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders