Vehicle and machinery sale

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/02/2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/01/2026 ዝግ ጨረታ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በድጋሚ ግልጽ ጨረታ በሎት የተዘረዘሩትንና በባንኩ ካፒታል ዕቃዎች ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ሰነዳቸውን ማግኘት የሚቻል ሲሆን እነዚህን

  • የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ/ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ያላቸው፣ የቀረጥ ነጻ ፈቃድ/መብት ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚሳተፉበትን የጨረታ ሎት የመነሻ ዋጋውን ዋጋ 25% (ሀያ አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በባንኩ 3ኛ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
  4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት፣ ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  5. የተዘረዘሩትን እቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በአስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. ማሽነሪዎቹን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ገላን ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
  7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለተጨማሪ ማብራሪያ- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የካፒታል ዕቃዎች ግዢና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥር፡ +251-11 524-4490 ወይም ኢ-ሜይል: [email protected]  መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-19
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-06-19 09:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (May 26, 2026)
  • Posted at: 2026-05-26T10:03:22.000Z
← Back to all tenders