በምዕ/ጉጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የሚገኘውን የተለያዩ ቢቢኤም ማረሻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕ/ጉጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የሚገኘውን የተለያዩ ቢቢኤም ማረሻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፤ ሆናም ግን ብረታ ብረቶቹን በአካል ማየት ከፈለጉ ቡ/ዙ/ወ/ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 1/2018 ዓ.ም ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆነ በታሸገ ፖስታ ዋና እና ፎቶ ኮፒውን ቡ/ዙ/ወ/ገ/ ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ሰኔ 1/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል። ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት የአንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0237 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
14. ሌሎች በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ሃሳቦች በግዥ መመሪያችን ቁጥር 1/2003 እና በሌሎች በተሻሻሉ የግንባታ የግዥ መመሪያዎች የምንገዛ ይሆናል።
የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-06-09 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Burie Localities FEDB
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 25, 2026
- Posted at: 2026-05-26T10:09:27.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.