Property and building foreclosure

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የቦታው ስፋት 202.5 ካሬ ሜትር የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ


በፍ/ባለመብት ፀደይ ሆቴል የሚጣል እቁብ ማህበር እና በፍ/ባለ እዳ ታደለ ታረቀ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በሺንዲ ከተማ ቀበሌ 01 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የፍርድ ባለ እዳ ንብረት የሆነውን በአዋሳኙ፡ - በምሥራቅ ገነቱ ጌታሁን፣ በምዕራብ ጌጡ ወለላው፣ በስሜን በልስቲ ሞላ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መጠኑ 202.5 ካሬ ሜትር የሆነውን በካርታ ቁጥር 1333/መ/ር-1 የተመዘገበ የግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 1,103,250 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሀያ አምስት ብር) ሆኖ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም 4፡00 እስከ 7፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል ስለዚህ የባለ እዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ ከሸያጩ ገንዘብ ውሰጥ ቢቻል ሙሉውን ካልተቻለ ¼ ኛውን በፍርድ ቤቱ በሞዴል 85 ማስያዝ ያለበት መሆኑን እናስታውቃለን።


የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid opening: 2026-06-24 13:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: West Gojam Zone Higher Court
  • Published on: Be'kur (May 25, 2026)
  • Posted at: 2026-05-26T10:34:55.000Z
← Back to all tenders