Property and building foreclosure
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት መኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ ሙላት ንጉሴ የሚጣል እቁብ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ 1ኛ. እንግዳ ዘለቀ፣ 2ኛ. ዘውዱ አበበ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሳሾች የተወሰነባቸውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ክፍት ቦታ እንዲሁም በደቡብ አየሁ ፈንቴ መካከል ያለውን በአቶ እንግዳ ዘለቀ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,735,259.12 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም) ይሸጣል። እንዲሁም 2ኛ. ተከሳሽ በአቶ ዘውዱ አበበ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ጠጀ ሙላት፣ በምዕራብ ሰለሞን ቁሜ፣ በደቡብ መንገድ፣ በሰሜን የሸ ቁሜ መካከል ያለውን መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,047,797.39 (አንድ ሚሊዮን አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ከሰላሳ ዘጠኝ ሳንቲም) ፍ/ቤቱ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ስለሆነም የጨረታውን ማስታወቂያ በጋዜጣ ለ30 ቀን እንዲውል በማድረግ የጨረታው ቀንም ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 እንዲሆን ፍ/ቤቱ አዝዟል።
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-25 11:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Guagesa Skudade Woreda Court
- Published on: Be'kur (May 25, 2026)
- Posted at: 2026-05-26T10:48:02.000Z