የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት ቤት መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ ሙላት ንጉሴ እቁብ ማህበር እና በአፈፃፀም ተከሳሽ 1ኛ. አቶ አክሊሉ አላምረው፣ 2ኛ. አቶ ማተቤ አሸንፍ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ ተከሳሾች በፍርዱ መሰረት መፈፀም ባለመቻላቸው ምክንያት በቲሊሊ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መቅደስ፣ በምዕራብ አበበ አላምነህ፣ በሰሜን ሙሉነሽ ከፍሌ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ በአቶ አክሊሉ አላምረው ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት መነሻ ዋጋ ብር 1,586,475.40 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰባ አምስት ብር ከአርባ ሳንቲም ይሸጣል። እንዲሁም የ2ተኛው አፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ልቅና ክንዴ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ በአቶ ማተቤ አሸንፍ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት መነሻ ዋጋ ብር 1,402,665 45 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም) የሁለቱም አፈፃፀም ተከሳሾች ቤት ከላይ በተገለፀው ግምት መሰረት ተደርጎ የጨረታ ማስታወቂው ከግንቦት 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ሰኔ 19/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡00 ድረስ የሚከናወን በመሆኑ ተጫራቾች የግምቱን ¼ ተኛው ገንዘብ ቀድሞ በሲፒኦ አስይዘው በእለቱ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል።
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-26 11:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Guagusa Shekudad Woreda Court
- Bid bond: 25%
- Published: May 25, 2026
- Posted at: 2026-05-26T10:50:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.