በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሠራተኞች ክበብ ካፍቴሪያ (የካፌቴሪያ የመሥሪያ ቦታ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፦ 009/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተሉትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-

ሎት አንድ የሠራተኞች ክበብ ካፍቴሪያ (የካፌቴሪያ የመሥሪያ ቦታ፣ ውኃ እና መብራት ነጻ ሆኖ ክፍያ የማይፈጸምባቸው ሲሆን ወጪው በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሚሸፈን ይሆናል። በተጨማሪም ተጫራቹ ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ሙሉ ቁሳቁሶችን እና የካፍቴሪያ መገልገያ ዕቃዎች አሟልቶ መግባት የሚችል መሆን ይኖርበታል)

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ኘሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎኘ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የሥራ ቀን) በ4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ብር ከሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ C.PO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። C.P.O መሥራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚልአድራሻ መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 11፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ/ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 1ዐ% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።

8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።

9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011 557 5742 / 011 557 5719 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-04 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የሥራ ቀን) በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Revenues Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: May 26, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T11:30:20.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders