የኮንደሚኒየም ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በፍ/ባለዕዳ በቀለ ለማ ወይም አቶ ሻሚል መሀመድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ መ/ቁ.220059 በ03/04/2011 ዓ.ም እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.247362 በቀን 17/06/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በፍ/ባለዕዳ አቶ ሻሚል መሀመድ ሀሰን ስም የተመዘገበ ኮንደሚኒየም ቤት መለያ ቁጥሩ AA0000610072901410428 የሰሪያል ቁጥር 067792 ካርታ ያለው የቤቱ ስፋት 46.07ካ/ሜ 2.34 ካ/ሜ የጋራ መጠቀሚያን ጨምሮ የሆነ የሐራጅ መነሻ 1,549,942.97 ( አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሁለት ከ97/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ሲሆን የዋስትና ፈንድ ሻጭ የሚከፍል ሲሆን የአደጋ ጊዜ ፈንድ መቋቋሚያ ሻጭና ገዢ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-29 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T08:24:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.