የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር_36/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4 (1) መሠረት፤
- የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣
- አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
- የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች እና
- ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ግቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
3. ያገለገለ ተሽከርካሪ(ሞተር ሳይክል) ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል።
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ የሐራጅ ጨረታው ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ/ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሔደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራች ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፣
7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም። በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
9. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታዉ ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96 /046-212-65-95
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Publishing entity: Hawassa Custom Commission Branch Bureau
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: May 27, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.