ስፋቱ 448 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ናርዶስ ግርማ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሸዋንግዛው ተክሉ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/09457 በ28/11/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/14870 በ20/02/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ፍርድ ለማስፈጸም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ውስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር ቦሌ7/31/7/11/8439/248099/01 በእነ አለሚቱ ዳቢ አባጨብሳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤትና ይዞታ የቦታው ስፋት በካርታው መሰረት 448 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 25,652,008 ( ሃያ አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ ¼ ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-06-29 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T10:30:34.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.