የቦታው ስፋት 161 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት የህፃን ዮሴፍ አምዴ (ሞግዚት መቅደስ ደሳለኝ) እና የፍ/ባለዕዳ አሰገደች ወርቅነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/114858 በ30/07/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/117741 በ9/10/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ፍርድ ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ ፍርድ ያረፈበት ቤት በቀድሞው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ቀበሌ 10/10  በአሁኑ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 009 የቦታው ስፋት 161 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 7,806,959 (ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼  ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-06-29 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 27, 2026
  • Posted at: 2026-05-28T10:32:40.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders