በቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ለቀጠሮ የህግ እስረኞች ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የወጥ ጥራጥሬ እህሎች፣ የምግብና የወጥ ማጣፈጫዎች፣ አትክልቶች፣ ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ሰርገኛ ጤፍ፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የፍርኖ ዱቄት እና የባህር ዛፍ የማገዶ እንጨት ለስድስት ወር ግዜ ውስጥ አጠቃሎ ለማስገባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ለቀጠሮ የህግ እስረኞች ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የወጥ ጥራጥሬ እህሎች የምግብና የወጥ ማጣፈጫዎች አትክልቶች ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ሰርገኛ ጤፍ፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የፍርኖ ዱቄት እና የባህር ዛፍ የማገዶ እንጨት ለስድስት ወር ግዜ ውስጥ አጠቃሎ ለማስገባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሱ ከዚህ በታች የሚከተሱትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፤
6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፣፣
8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታበማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሎድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
10.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
11. ጨረታው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12.ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በአጋጣሚ ምክንያት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር+-0114716333/0118886089/0114348986 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-06-12
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-06-12 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Prisons Administration Facility House Administration
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 28, 2026
- Posted at: 2026-05-28T10:39:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.