የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን የሚዛን አማን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 ዓመት ለመከራየት ይፈልጋል

Description

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን የሚዛን አማን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 ዓመት ለመከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

መስፈርቶቹም ፡-

1. ከ9 እስከ 10 ክፍል ወይም ከ150 እስከ 200 ካሬሜትር በላይ ስፋት ያለው ሆኖ ቢያንስ እያንዳንዱ ክፍል ከ 3×4m2 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከዚህ ውስጥ ሁለት ክፍል ከ5X7m2 በላይ የሆነ፣

2. ቤቱ ውሃ፣መብራትእና ሽንት ቤት ኖሮት ህንጻ ከሆነ መነሻ G+0 ሆኖ መጨረሻው ከG+2 በላይ ያልሆነ፣

3. ይህን ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች ከሚዛን አማን ከተማ ከአሰፋልቱ መንገድ በግራ እና ቀኝ እስከ 200ሜ ገባ ብሎ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ፣

  • ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆናችሁ የቫት ሰርትፊኬቱን ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን የምትሰጡት ዋጋ ቫት ማካተትና ያለማካተት በግልጽ መግለጽ ያለባችሁ ሆኖ ይህ ሳይገለጽ ከቀረ ያቀረባችሁት ዋጋ ቫት ያከተተ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
  • ተወዳዳሪዎች ቤቱ ህጋዊ ስለመሆኑ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፣
  • ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጥዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ሚዛን አማን ቅርንጫፍ ቀርበው በመገዛት የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
  • ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛ የስራ ቀን ከሰዓት በ8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
  • ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

ስልክ +251-47-135-0032 / 09 17-82-86-19

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሚዛን አማን ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-08
  • Publishing entity: የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕ/ሪጅን የሚዛን አማን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: May 27, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders