የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የመጀመሪያ (1ኛ) ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ክፍያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት ኪራይ ለመክፈል ፍቃደኛ ባለመሆኑ በባንኩ ስም ተመዝግበው ደንበኛው ተከራይቶ የነበረውን እና ባንኩ ከተከራዩ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎች በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል ዕቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በመጀመሪያ (1ኛ) ዙር በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
|
ተ.ቁ |
የተከራዩ ስም |
የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር) |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
የሐራጁ ደረጃ |
|
1 |
አቶ ሊሬ ጊቦሬ የዳቦ ማምረቻ ማሽን |
1. Rotary Over 16 Try የዳቦ ማኮፈሻ አንድ (01) set 2. Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set 3.Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4.Proofer for rotary oven with steam generator (01) set 5.Molding machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 6. Brade slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) set 7. French bread tray and rottey for ATDF250 ሁለት (02) set 8. Flat tray with trolley for ATDF 250 ሁለት (02) 9. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው። |
በቀድሞ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በ ጀሎናረሞ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሊሬ ጊቦሬ (የተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ |
9,557,411.54 |
በቀድሞ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በጀሎናረሞ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሊሬ ጊቦሬ (የተከራዩ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ |
ሰኔ 25 2018 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00
|
1ኛ |
|
2 |
አቶ ሱማሞ ዶባሞ የዳቦ ማምረቻ ማሽን |
1. Rotary Over 16 Try የዳቦ ማኮፈሻ አንድ (01) set 2. Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4Proofer for rotary oven with steam generator (01) set 5.Molding machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 6. Brade slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) set 7. French bread tray and rottey for ATDF250 ሁለት (o2) set 8. Flat tray with trolley for ATDF 250 ሁለት (02) 9. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው:: |
በቀድሞ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ |
9,729,235.52 |
በቀድሞ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (የተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤ |
ሰኔ 26 2018 ዓ.ም 4፡00 እስከ 6፡00
|
1ኛ
|
የሐራጅ መመሪያ
- የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ ¼ ኛ ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይቻላል። በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በማቅረብ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ የሐራጅ ጨረታው ይካሄዳል፤
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጅ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጅ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ በሐራጅ ጨረታ መሳተፍ ይችላል።
- የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽየጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል።
- በሐራጅ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ተያያዥ የሆኑ ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- በሐራጅ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው እጅ በእጅ በሚደረግ ሽያጭ/cash/ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሰራር በመከተል የሚደረግ ሽያጭ ይሆናል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሐራጁን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከጨረታው ቀን በፊት ባሉት ጊዜአት ቀጠሮ በመያዝ ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ንብረቶቹን በሚገኙበት አድራሻ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1528 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-03 12:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 25%
- Published: May 28, 2026
- Posted at: 2026-05-28T11:35:50.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.