የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሣሽ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ አሰፋ ሙሉነህ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈጻጸም ተከሣሽ ስም የተመዘገበ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) የሰሌዳ ቁጥር አማ-01-40830 ሞዴሉ ICON-X የሻንሲ ቁጥር MD9FP2B15K1275625 የሞተር ቁጥር FP1K6000709 የተሰራበት ዘመን 2019 የሆነ ባጃጅ ከአሁን በፊት በቁጥር 71004 በቀን 23/09/2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት እግድ ያለበት መሆኑና ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ በማስመርመር የሚጠበቅባቸውን የቦሎ ቅጣት እና የአገልግሎት ክፍያ ብር 12,121 /አስራ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃያ አንድ ብር/ ለመንግስት የሚከፈል ያለ መሆኑን አውቀው የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 212,874 /ሁለት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሠባ አራት ብር/ ንብረቱ በሚገኝበት በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና መስሪያ ቤት ደ/ብርሃን ከተማ በእምዬ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ንግስት እሌኒ ቀበሌ በሚገኘው በከሣሽ ዋና መ/ቤት ውስጥ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል።

በመሆኑም፡-

1. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሲፒኦ ለሀራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው።

4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል።

5, የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል።

የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-25
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-07-25 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone High Court
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T10:07:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders