Vehicle and machinery foreclosure
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የጨረታ ማስተካከያ አውጥቷል
Description
በመጀመሪያ ዙር የሐራጅ ጨረታ ላይ
ማስተካከያ ማድረግ ማስታወቂያ
ከባንካችን የተበደሩትን የብድር ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ካልሆኑ ተበዳሪዎች የተረከባቸውን የዋስትና ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በተከራይ የሆሳዕና ቅርንጫፍ የሊዝ ፋይናንሲንግ ደንበኛ የሆኑት አቶ ሱማሞ ዶባሞ የዳቦ ማምረቻ ማሽን ከባንኩ ጋር በገባው የካፒታል ዱቤ ኪራይ ግዥ ውል ስምምነት መሰረት ወቅቱን ጠብቆ የኪራይ ክፍያውን መክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ባንኩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በኪራይ ያስተላለፋቸውን የካፒታል እቃዎችን በህጋዊ መንገድ የተረከበ ሲሆን ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣው ማስታወቂያ የመጀመሪያ (1ኛ) ዙር የሐራጅ ጨረታ ብር 9,729,235.52 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለሽያጭ መውጣቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ በሐራጅ ማስታወቂያው ሰንጠረዥ “የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ” በሚለው ስር 1ኛ Rotary oven Try 16 የዳቦ ማኮፈሻ አንድ (01) set በሚል የተጠቀሰው ንብረት Rotary oven Try 16 (የዳቦ ባትራ) በሚል መቀመጥ ሲገባው የዳቦ ማኮፈሻ በሚል የተጠቀሰው የአማርኛ ፍቺ በስህተት የገባ መሆኑን፤ እንዲሁም 4ኛ Proofer for rotary oven with steam generator ተብሎ የተጠቀሰው ንብረት ሙሉ በሙሉ የሌለ በመሆኑ በስህተት የተጠቀሰ መሆኑ እየገለጽን ሌላው ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት መሆኑን እንገልጻለን።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6a1828960a538a96ea000001
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-03 12:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Published on: Addis Zemen (Jun 19, 2026)
- Posted at: 2026-06-19T07:21:00.000Z