አጠቃላይ ይዞታው 273 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሙሉጌታ አሰፋ እሸቴ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ እሸቴ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/262275 በ21/6/2015 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/300814 በ04/08/2015 ዓ.ም በ7/9/2015 ዓ/ም በ26/7/2015 ዓ/ም በ2/3/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 416 የሆነ ቤት ላይ ከዋናው ቤት ጀርባ ለብቻ የተሰራ ባለ ሁለት ክፍል ቤት 24.44 ካ.ሜ ግምቱ 879,962.2 (ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ብር 20/100) ሚሊዮን የውርስ ሀብት የሆነው ይዞታ የቦታ ስፋት 248.56 ግምቱ 6,616,002.8 (ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሁለት ብር 80/100) አጠቃላይ ይዞታው 273 ካ.ሜ ሲሆን የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 7,495,965 (ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አምስት ብር) የሰፈር መንገድ 21 ካ.ሜ ይነካዋል አዋሳኞች በሰሜን በደቡብ ታደለ ከበደ በምስራቅ መንገድ በምዕራብ ዕዳር ቤት ስመ ንብረቱ በአቶ አሰፋ እሸቴ እና በወ/ሮ እናት አበጋዝ ስም የተመዘገበ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.300814 በ30/08/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 1,873,991.25 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ዘጠን መቶ ዘጠና አንድ ከ25/100)ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ' ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-07-01 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 28, 2026
- Posted at: 2026-05-28T11:51:18.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.