ወጋገን ባንክ አ.ማ. የንግድ ህንፃ (B+G+7) ግንባታው 71/100 የተጠናቀቀ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ወጋገን ባንክ ኢማ
ቁጥር ወጋገን 027/2017
ወጋገን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መስረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ንብረት አስያዥ |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ |
የይዞታው አገልግሎት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚከናወንበት ጊዜ |
|||
|
ክልል |
ከተማ ክ/ክተማ |
ወረዳ/ ቀበሌ
|
ቀን |
ሰዓት |
||||||||
|
1 |
ገ/ትንሳኤ ገ/እግዚኣብሄር |
ገ/ትንሳኤ ገ/እግዚኣብሄር |
ገርጂ
|
ትግራይ |
ማእከላዊ ዞን |
ዓድዋ |
2,415 ካ/ሜትር |
19/6/201
|
የንግድ ህንፃ (B+G+7) ግንባታው 71/100 የተጠናቀቀ |
198,569,851.09
|
ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. |
ከጧቱ 3:00-6:00 ስዓት ድረስ |
ማሳሰብያ
1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) በወጋገን ባንክ አማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በአካል በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
2. የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 አስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
3. በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በውስጥ መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል።
4. የተጫራቾች የምዝገባ ስዓት፣ ከጧቱ 3፡00 - 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው። ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል።
5. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
8. ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
7. ጨረታው የሚካሄደው በአድዋ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ዓድዋ ቅርንጫፍ ይሆናል።
9. ተበዳሪው/ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል። ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው
10. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል።
11. ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-1837፤ የሽሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፡ 034-244-3685/ 034-244-4248 እና የዓድዋ ቅርንጫፍ፡ 034-771-4046/ 034-771-4043 መደወል ይቻላል።
12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ወጋገን ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 09:00
- Bid opening: 2026-06-26 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Wegagen Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T12:59:30.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.