የቤት ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ፀደይ ባንክ ሳሊ ቅርንጫፍ እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ. አደራጀዉ ወርቁ 2ኛ, ብርቱካን መብሬ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በላይ ጋይንት ወረዳ ጎብጎብ ከተማ በአዋሳኝ በምስራቅ አሰፋ ደጀን፣ በምእራብ አስቻለ ንጋቱ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ዋና መንገድ የይዞታ መጠኑ 336 ካ/ሜ በኛ አፈ/ተከሳሽ ስም በአቶ አደራጀው ወርቁ ንብረት የሆነ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋው ብር 1,255,820 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ብር/ ሲሆን መጫረት የሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች መጫረት የሚችል መሆኑን እየገለፅን ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከግንቦት 21 ቀን 2018 ዓም እስከ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ለ30 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ሠዓት ባለው ጊዜ ዉስጥ ተከፍቶ አሸናፊው ከተለየ በኋላ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታው ያሸነፈበትን ዋጋ 1/4ኛውን /25%/ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እና ቀሪ ገንዘቡን ደግሞ በ15 ቀናት ውስጥ ከፍሎ የሚያጠናቅቅ ይሆናል። ጨረታው የሚካሄድበት ወቅትም የጎብጎብ ከተማ አስ/ጽ/ቤት የጎብጎብ ከተማ ምድብተኛ ፖሊስ እና የፍርድ ቤቱ ሃራጅ ባይ በአንድ ላይ በመሆን እንድትጫረቱ ሲል ፍ/ቤቱ አዟል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-28
- Bid closing time: 12:30
- Bid opening: 2026-06-28 12:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: South Gonder Zone High Court
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T07:53:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.