የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ባንቺአየሁ ቢያርግልኝ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አጸደ ለማ ሁንዴ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 190857 በቀን 24/5/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ቀበሌ 12 በአዲሱ ወረዳ 02 ውስጥ በፍ/ባለዕዳ ስም የሚታወቅ ስም የቤ ቁ 665 የሆነ ቤትና ይዞታ ካርታም ሆነ ደብተር የሌለው ሰነድ አልባ በ1988 ዓ.ም በተነሳው የአየር በረራ ፎቶ (Gls) (ጂአይ ኤስ)መረጃ መሠረት በብሎክ ቁጥር 24 በፓርሴል ቁጥር 10 በተገኘው መረጃ መሠረት ጠቅላላ የቦታው ስፋት 2070 ካ.ሜትር ቤቱ ይዞታ) በፕላን ተቃርኖ ውስጥ የሚገኝ እና በአሁኑ ሰዓትም ሀገራዊ ልማት በሆነው የጫካ ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኝ ይዞታው ለልማት የሚፈለግና የሚነሳ መሆኑን አዋሳኙ በሎሜን መንገድ፤ በደቡብ የመንግስት ዳር ጫካ ፤በምስራቅ ቆንጅት ሽፋው በምዕራብ ዝናሽ ገፈው የሚያዋስኑ ቤቱን በጨራታ የሚያሸንፍ አካል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአሁኑ ሰዓት በአገልግሎቱ ላይ በዋለው በደንብ ቁጥር 163/2016 ዓ.ም የመሬት ይዞታ መብት ፈጠራ አገልግሎት አሰጣጥ መሰፈርት መሠረት ተጠብቆ መስፈርቱን ካሟላ አገልግሎቱን የሚያገኝ ሲሆን መስፈርቱን ካላሟላ አገልግሎቱን የሚከለከል እና አስተዳደሩም ሃላፊነቱን የማይወስድ (የማይገደድ ) መሆኑን የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 16,404,282 (አስራ ስድስት ሚሊዬን አራት መቶ አራት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል።የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫጭርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አ ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-02 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: May 30, 2026
- Posted at: 2026-05-30T07:58:29.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.