የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል እና ሴቶች ማረፊያና ማረሚያ ቤት ማዕከል ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች አንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች፣ የማገዶ እንጨት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል እና ሴቶች ማረፊያና ማረሚያ ቤት ማዕከል የምግብ ጥራጥሬ ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት፤

የጨረታ ቁጥር-1- ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች አንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት፤ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፤ በሥራ መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢ አገልገሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የተጨ ማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዲሁም ቲን ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር ስለመክፈላቸው የተሟላ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ለህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች አንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች፣ የማገዶ እንጨት ለጨረታው የውል ማስከበሪያ ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።

4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፕሮፎርማቸው) በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ4 ኮፒ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ ቁጥር 1- ሰኔ 08/10/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዥ ከንውን ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ገላን እና ቃሊቲ ሴቶች ማረ/ማዕከል በሚገኘው ገ/ቤታችን ማስረከብ አለባቸው፤ ማረ/ቤቱ የሚገዛቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝረው ቀርቧዋል።

8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁፕር 1000007971188 ቃሊቲ ማረ/ቤት እደ/ጥ/ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኋላ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

10. ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲፅፉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

ከፍተኛ ጥ/ማረ/ማዕከል

ገላን

በስልክ ቁጥር-- 011-462-4043/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-15 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል
  • Bid bond: 60,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: May 30, 2026
  • Posted at: 2026-05-30T08:13:23.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders