የተለያዩ ቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ሃና እዝራ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ የውብዳር ሸዋዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/96303 24/8/2015 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/119761 በ16/08/2017 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/119761 በ12/10/2017 በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ሰንዳፋ በኬ ከተማ ቀበሌ 01 ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር 09/107/58 የሆነ ይይዞታ ስፋት 2000ካ/ሜ ካርታ ያለው ከአጠቃላይ ይዞታ ላይ በኮሪደር ልማት 295ካ/ሜ የሚነካው ሆኖ በአሁኑ ሰዓት የኮሪደር ልማት የተተገበረ ሲሆን ቀሪ የይዞታ ስፋት 1705 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,990,920 ( አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 1811 ስፋቱ 540ካ/ሜ የካርታ ቁጥር 036285 የተመዘገበ ካርታ ያለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 32,412,540 ( ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አርባ) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-01 14:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 30, 2026
  • Posted at: 2026-05-30T08:31:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders