የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ የ2018 በጀት የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጪ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/ የተ የግ ማህበር የ2018 በጀት የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጪ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል
1. በኦዲት ስራ ፈቃድ ያለው እና የሙያ ብታት ማረጋገጫ ያለው፣ እዲሁም የግድ ሥራ ፈቃዱን በዘመኑ የታደሰ፣
2. የቲን ነምበር፣ የቫት እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን የ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
4. የኦዲት ስራው የሚከናወነው በ IFRS እና በ GAAP የሪፖርት አሰራር መሰረት መሆን አለበት።
5. የጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፤
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ በድርጅታችን ስም ማስያዝ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
8. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
9. ማንኛውም ተጫራች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
11. የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12. ተጫራቹ የአገልግሎት ዋጋውን ሲሞላ ለሚያሰማራቸው ባለሙያዎች የትራንስፖርት፣ አበልና የተለያዩ የመስተንግዶ ወጪዎችን ታሳቢ አድርጐ መሙላት አለበት።
13. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፣
14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
15. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 36 84 37/09 10 19 31 73 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-06-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debrhe Berhan Wood Processing P.L.C
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: May 30, 2026
- Posted at: 2026-05-30T08:36:25.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.