የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase 1 ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለምርት ማሳያ ቦታ፣ ጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና 2 ሱቆች የሚፈልጉትን ምርት ወይም አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በኪራይ መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T619

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase 1 ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለምርት ማሳያ ቦታ፣ ጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና 2 ሱቆች የሚፈልጉትን ምርት ወይም አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በኪራይ መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል በዘርፉ ለመስራት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር/አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E -99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T619 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
  3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid security) አንድ መቶ ሺህ ብር (ብር 100,000) ለሁለቱ ሱቆች (ሱቅ 3 እና 5) ፣ አንድ መቶ ሺህ ብር (ብር 100,000) ለጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ ሱቅ እና ሀያ አምስት ሺህ ብር (ብር 25,000.00) ለምርት ማሳያ አገልግሎት የሚውል ቦታ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም የተገኘ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
  4. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት 5:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-8953

ወ/ሮ ጠይሜ ተሰጋ

ኢ-ሜይል: TeymeT@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Ethiopian

የኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-06-17 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 01, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T11:29:20.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders