ግሎባል ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05-2025/26
ግሎባል ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዥ ላይ የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች በመገንዘብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
Nissan Pick Up 4WD |
4 |
|
2 |
Nissan Almera Automatic Transmission |
4 |
|
3 |
Toyota RAV4 Automatic Transmission 4WD |
2 |
|
4 |
Nissan X-trial Automatic Transition 4WD |
1 |
|
5 |
Nissan Micra Hatch Back |
2 |
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢማ ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7 ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 5፡45 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 10፡45 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 5፡45 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
2. የጨረታ መነሻ ዋጋቸው እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንኩ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢማ ስም በማስራት እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኘውን ቅጽ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎኘ እስከ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንጻ 7ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ሰዓት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
4. የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቶቹን ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት በአግባቡ ተመልክተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል።
6. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7 ለበለጠ መረጃ፡- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ስስክ ቁጥር 011 558 1204 ወይም 011 531 8156 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Publishing entity: Debub Global Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 31, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.