በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ጉዳይ ችሎት የቤት ሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

1ኛ የጨረታ ማስታወቂያ

በአፈፃፀም ከሳሽ ሽመልስ አምሣሉ ኦሊቃ እና የአፈፃፀም ተከሳሽ ፍቅርተ ኃይሉ ደሜ መካከል ያለውን የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ በተመለከተ ካርታ ቁ OR007034204004 የሆነው ስፋቱ 88.08 ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ ሠፍሮ በቡራዩ ክ/ከተማ ገፈርሳ ቡራዩ ወረዳ ውስጥ በአቶ አበራ ቶላ ጎሮ ሥም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 589044.72 (አምስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ አርባ አራት ብር ከ 72/100) ከ27/09/2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 27/10/2018 ዓ.ም. በአየር ላይ ቆይቶ በ29/10/2018 ዓ.ም. በተገኘው ከፍተኛ ዋጋ ከጠዋቱ 03፡00 ሠዓት እስከ 06፡30 ሰዓት የሚሸጥ በመሆኑ፣ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የጨረታ መነሻን ዋጋ 1/4ኛ ሲፒኦ በማስያዝ ተወዳድራችሁ እንድትገዙ የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳውቃል።

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ጉዳይ ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-07-06 12:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Sheger City High Court
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 01, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T12:02:29.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders