ሕብረት ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ንብረቶችን በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ይሸጣል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/02 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ይሸጣል።

ተቁ

የተበዳሪ ስም

 

የአስያዥ ስም

የቅርንጫፍ ስም

 

ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታው ስፋት

የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር

 

የሃራጅ መነሻ ዋጋ በብር

ሃራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰአት

1

በርሀቦት የምግብ ማምረቻ ኃላ የተ.የግ.ማህበር

 

አቶ ሲራክ ብርሃኑ ፈይሳ

 

ሃያ አራት

 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የካ /ከተማ ወረዳ 12 የቦታው ስፋት 1,315 ካ.ሜ የሆነ መጋዘን፤

AA000051203914

 

33,368,076.88

ሰኔ 25 ቀን 2018 አ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰአት

2

ዳስ ኢንጂነሪንግ እና ኢኖቬሽን /የተ/የግ/ማህበር

 

አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ ከበደ

 

ቦሌ መድሃኒዓለም

 

አዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ /ከተማ፣ ወረዳ 02 የቦታ ስፋት 500 ካሜ የሆነ G+2 (ባለሁለት ፎት) መኖሪያ ቤት

AA000080205818

 

76,543,968.14

ሰኔ 25 ቀን 2018 አ.ም ከሰአት 8፡00 እስከ 9፡00 ሰአት

3

ወ/ይ ኤልሳቤጥ ባለው ካሳ

 

ወ/ይ ኤልሳቤጥ ባለው ካሳ

 

የሺ ደበሌ

 

ኦሮሚያ ክልል፣ በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ በአሁኑ ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ መና አቢቹ /ከተማ፣ አትሌቶች ሰፈር፣ የቦታው ስፋት 140.74 ካሜ የሆነ መኖሪያ ቤት

OR00002031611012

 

3,927,200.41

ሰኔ 26 ቀን 2018 አ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰአት

4

ወ/ይ ኤልሳቤጥ ባለው ካሳ

 

ወ/ይ ኤልሳቤጥ ባለው ካሳ

 

የሺ ደበሌ

 

ኦሮሚያ ክልል፣ በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ በአሁኑ ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ መና አቢቹ /ከተማ፣ አትሌቶች ስፈር፤ የቦታው ስፋት 216.66 . የሆነ መኖሪያ ቤት

OR00002031110043

 

5,432,624.77

ሰኔ 26 ቀን 2018 አ.ም ከሰአት 8፡00 እስከ 9፡00 ሰአት

5

አመንድ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

 

አቶ ደመቀ ሞሌ ባንቴ

 

ልደታ

ኦሮሚያ ክልል፣ በቀድሞ ሱሉልታ ከተማ በአሁኑ ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ መና አቢቹ /ከተማ፣ አትሌቶች ሰፈር፣ የቦታው ስፋት 200 . የሆነ መኖሪያ ቤት፣

Sul/2615/12

 

3,262,031.67

 

ሰኔ 26 ቀን 2018 አ.ም ከጠዋቱ 7፡00 እስከ 8፡00 ሰአት

6

አመንድ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

 

አመንድ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

 

ልደታ

አማራ ክልል፣ ደብረብርሀን ከተማ፣ ጫጫ /ከተማ፣ ወረዳ አን/ጠረ፣ ቀበሌ 01 የሚገኝ ለኢንዱስትሪ/ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የቦታው ስፋት 7,020 . የሆነ በግንባታ ላይ ያለ ቤት/መጋዘን፤

2641/13

40,095,154.19

ሰኔ 29 ቀን 2018 አ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰአት

7

ሙሉጌታ እና ቤተሰቡ ኃላ/የተ/ የግ/ማህበር

 

ሙሉጌታ እና ቤተሰቡ ኃላ/የተ/ የግ/ማህበር

 

ልደታ

ኦሮሚያ ክልል በቀድሞ ቡራዩ ከተማ በአሁኑ ሸገር ከተማ መልካ ኖኖ / ከተማ፣ የቦታው ስፋት 566 . የሆነ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል መጋዘን፤

Bur/570/97

 

7,453,788.76

 

ሃምሌ 01 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

 

የሐራጅ ደንቦች፡-

1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።

2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል።

3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው። ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆነ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ዕ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።

4. ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው። ከተራ ቁጥር 3-7 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ ደግሞ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው።

5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።

6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።

7. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ንብረቶች ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ እስከ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።

8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።

9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 470 6380/ 011 466 6593 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-08 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hibret Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: May 31, 2026
  • Posted at: 2026-06-02T12:46:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders