በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ከሃምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ የሚቆይ የተለያዩ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሠራት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 01/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ከሃምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ የሚቆይ የተለያዩ አገልግሎቶች
ማለትም፦
- ሎት 1. የጽዳት አገልግሎት/Out source/
- ሎት 2. የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቢስ አገልግሎት
- ሎት 3. የደረቅ ጭነት አገልግሎት
- ሎት 4. የመኪና ጥገና አገልግሎት
- ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /tin /ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4. የጨረታ ሰነዱን በብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ የስ/ሒደት ቢሮ መውሰድ ይቻላል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ያክሉን ለሆስፒታሉ በCPO/በመሂ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
6. ከብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ለሚገዙ አገልግሎቶች 3% የመቁረጥ እና በሥማቸው የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።
7. አሸናፊ ሆኖ የሚገባው ተጫራች የፅዳት አገልግሎቱን ለ 24፡00 ሰዓት ሳይቆራረጥ መስጠት አለበት። በመሆኑም የዕዳት ቋሚና አላቂ ግብአቶች በወሩ መጀመሪያ 1–3 ባሉት ቀናት ውስጥ ማስገባት አለበት።
8. የሰራተኛ ሰርቢሱ 28 ወንበርና ከዚያ በላይ ያለው ደረጃ አንድ ቅጥቅጥ መሆን አለበት።
9. የተሸከርካሪው የስምሪት ዘመን/የምርት ዘመን እ.ኢ.አ ከ2013 ወዲህ የተመረተ አዲስ ሞዴል መሆን አለበት።
10. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎች እና የናፍታ ክፍያ በራሱ በተጫራቹ ነው።
11.ተሽከርካሪው ሙሉ ቀን ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚሠጥ መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
12. የተሸከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት እንዲሁም የቴክኒክ ምርመራ/ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት።
13. ተሸከርካሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት።
14. ለሁሉም ሎቶች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ሥማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
15. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በ C.PO በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት።
16. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክመንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
17. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎበዚያው ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል።
18. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ እና ሠዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በሆስፒታሉ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም።
19. ለሁሉም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋው መሙሊያ ላይ ማግኘት ይቻላል።
20. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ /ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀናት ይከፈታ።
21. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
22. ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 09 20 20 56 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡ - በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምእራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-06-16
- Publishing entity: Shewa Robit Elementary Hospital
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 01, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.