በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር የህትመት ስራዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያዎች /የመመገቢያ እቃዎች/፣ የቤት ውስጥ የህፃናት መጫወቻዎች እና የቢሮ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የቀበና ጤና ጣቢያ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር በጨረታ ቁጥር ቀ/ጤ/ጣቢያ 4/2018 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ህትመት፣ የቤት ውስጥ መገልገያዎች የመመገቢያ እቃዎች/ የቤት ውስጥ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የቢሮ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር የቀ/ጤ/ጣ 04/2018 ዓ.ም

  • ሎት 1. የህትመት ስራዎች
  • ሎት 2. የቤት ውስጥ መገልገያዎች /የመመገቢያ እቃዎች/ የቤት ውስጥ የህፃናት መጫወቻዎች
  • ሎት 3. የቢሮ እቃዎች
  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀበና ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ 4,000.00 /አራት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራቾች ሰነዱን ለማስገባት በሚመጡበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያሥፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል አብሮ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን ከሲፒኦ ጋር በአንድ ፖስታ እና ኮፒ ሰነድ በሌላ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ማህተም በማድረግና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30- 11፡00 ሰዓት ድረስ የጤና ጣቢያው የግ/ን/አስ/ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ በቀበና ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫት አካቶ መሆን አለበት።
  7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራቾች በተመዘገቡበት ንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መወዳደር አለባቸው::
  8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ እስከ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል። በዚህ አንቀጽ በተገለፀው መሰረት እቃዋቹን ያላስገባ ካሸነፈበት ጠቅላላ ብር ላይ በየእለቱ 0.01% ተቀናሽ እንደሚደረግ እናሳስባለን።
  9. የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም። ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ ቀበና የኦሮሚያ ደን ልማት ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 011-8-11 21 55 / 0111  23 56 07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት

የቀበና ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-13 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Sub City Kebena Health Care Office
  • Buyer address: ቀበና ሼል ከመድረሱ በፊት የኦሮሚያ ድን ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና ምሥራቅ ፀሐይ መድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ
  • Bid bond: 4,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T08:27:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders