የተለያዩ ቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለሙበት ወ/ሮ የሮምነሽ ተገኝ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ አሸናፊ ጉጃ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.85630 በ11/08/2014ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 21/11/2014ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 20/3/2015ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት

1ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 450 ቁጥር 18/72/25/046/00 የተመዘገበ ተነጻጻሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ የቦታ ስፋት 749ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት 344.72ካ/ሜ ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 217.28 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደረሰው የቦታ ስፋት 562 ካ/ሜ ከጠቅላላው ይዞታ ላይ የመንገድ ጥናት 97 ካ/ሜ ይነካዋል ይዞታው LDP Relocaion site ለመልሶ ማስፈሪያ የተያዘ ነው የሐራጅ መነሻ 14,011,646 (አስራ አራት ሚሊዮን አስራ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አራባ ስድስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 451 ካርታ ያለው ተነጻጻሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ የቦታ ስፋት 538ካ/ሜ ቤቱ ነገር ግን በቀን 10/07/2004 ወጪ የሆነው ካርታ በፕሮፖርሽን ያደረገው በመሆኑ ቤቱ ከጠቅላላው በፕሮፖርሽን የሚደርሰው 187ካ/ሜ ከጠቅላላው ይዞታ ከቤት ቁጥር 450 እና 451 ላይ የመንገድ ጥናት 97 ካ/ሜ ይነካዋል ይዞታው LDP Relocation site ለመልሶ ማስፈሪያ የተያዘ ነው የሐራጅ መነሻ 7,015,371 ( ሰባት ሚሊዮን አስራ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አንድ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25111 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ሰአት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-07 15:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ሰአት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T08:36:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders