የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ራሄል ፍቅሩ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ዳኛቸው አያህሉህም መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/ 150477 በ22/10/2013 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/175279 በ14/11/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት
1ኛ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 በእንይ ሪልእስቴት ብሎከ K2 የቤት ቁጥር 101 የሆነው መኖሪያ ቤት ቦሌ 12/44/4/245559/00 በእንይ ሪልእስቴት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የቤቱ ስፋት 112 ካ/ሜ ካርታ ያለው የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,593,344 ( አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አራት) የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በቦሌ ከ/ከተማ ሰሚት ሳይት ወረዳ 16 የካርታ ቁጥር ቦ/ክማ/366/11630/04 በሴርያል ቁጥር 041315 በቀን 12/06/2004 ዓ/ም የተሰጠ ካርታ ያለው ባለሁለት መኝታ ቤት የቤቱ ስፋት 66.56 ካ/ሜ በፐሮፖርሽን 62.70 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,131,051.52 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሃምሳ አንድ ብር ከ52/100) የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
3ኛ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 በእንይ ሪልእስቴት ብሎክ K2 የቤት ቁጥር 101 ውሰጥ የሚገኝ ንብረት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 84,450(ሰማኒያ አራት ሺ አራት መቶ ሃምሳ ብር) መሆኑ ታውቆ ሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-03
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-03 11:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 02, 2026
- Posted at: 2026-06-03T08:52:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.