የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የሰራተኞች መዝናኛ ክበቦቹን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በማወዳደር በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድሰመክ/ብግጨቁ/11/2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበቦቹን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በማወዳደር በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid lrade License)፣

2. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣

3. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣

4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣

5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) 6ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ህጋዊ ሰነዶች፣ የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ ማስከበሪያ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ 6ኛ ፎቅ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።

 ማሳሰቢያ፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስልክ ቁጥር፡ 0922 536 049

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-29 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Organization
  • Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T09:17:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders