የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ የውብፀሀይ አፈወርቅ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወንድወሰን አፈወርቅ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/96322 በ6/02/2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/100422 በ15/5/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ ፍርድ ያረፈበት ቤት በጉለሌ ክ/ከተማ በቀድሞው ቀበሌ 02 በአዲሱ ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 870 የካ/ቁ/11684 በአቶ አፈወርቅ ደስታ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ 901 ካ/ሜ ሲሆን ቤቱ አሁን ባለው ጥናት መንገድ 26.45 ካ/ሜ የሚነካው ላይ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 24,130,960 (ሀያ አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰለሳ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ብር ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.100422 በቀን 20/8/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 6,032,740 ( ስድስት ሚሊዮን ሰላሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አርባ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት/ ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-06
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-07-06 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 03, 2026
- Posted at: 2026-06-03T09:21:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.