ጸደይ ባንክ አ.ማ. ስፋቱ 200 ካ.ሜ. የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ፀደይ ባንክ /አ.ማ/ ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት

የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጸደይ ባንክ አ.ማ. ለአቶ ታደሰ አላምረው የሰጠው ብድር ባለመመለሱ ባንኩ በዋስትና /በመያዣ/ የያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በድሮው ቀበሌ 07 በአሁኑ ቀበሌ 12 በወ/ሮ ጥሩድል ታደሰ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 200 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2. የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 2,785,000 / ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ ብር / ነው።

3. በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፣ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።

4. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።

5. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው 1/4ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ፣እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ :: ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።

8. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

9. ጨረታው የሚካሄደው ደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 12 ለጨረታ በወጣው ንብረት ውስጥ ነው።

10. ጨረታው የሚካሄደው ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ይሆናል።

11.ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0921667115 /0912436868 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-07-07 12:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T12:42:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders