በቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ለቀጠሮ የህግ እስረኞች ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የወጥ ጥራጥሬ እህሎች የምግብና የወጥ ማጣፈጫዎች አትክልቶች ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ሰርገኛ ጤፍ፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የፍርኖ ዱቄት እና የባህር ዛፍ የማገዶ እንጨት ለስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ ለማስገባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ለቀጠሮ የህግ እስረኞች ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የወጥ ጥራጥሬ እህሎች የምግብና የወጥ ማጣፈጫዎች አትክልቶች ጥራቱን የጠበቀ ነጭ ሰርገኛ ጤፍ፤ የበቆሎ ዱቄት፣ የፍርኖ ዱቄት እና የባህር ዛፍ የማገዶ እንጨት ለስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ ለማስገባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን፣ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው

6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት። ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፣፣

8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሎድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል።

11. ጨረታው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።

13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በአጋጣሚ ምክንያት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

አድራሻ፡-ቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ስበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር+- 011 471 6333/ 011 888 6089/
011 434 8986 ደውለው መጠየቅ ይችላሱ።
የቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-06-12 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Abeba Correctional Facility Kilinto
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 05, 2026
  • Posted at: 2026-06-05T07:54:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders