የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አቶ ሀይሉ ኢብሳ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ገረመው ኢብሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 109160 በ16/11/2017 ዓ/ም በመ/ቁጥር 119597 በ25/3/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ /ከ/ከተማ ወረዳ 4 የቤት ቁጥር 446 የሆነ ቤት የመለያ ቁጥር AA000020400206 የተመዘገበ የተነጻጸሪ ካርታ ያለው የይዞታው ስፋት ጠቅላላ 581.58 ካ/ሜ ሲሆን የቤቱ ስፋት 175 ካ/ሜ ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው በተነጻጻሪ ድርሻ 251ካ/ሜ በጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለቤቱ የሚደረውሰው የቦታ ስፋት 426 ካ/ሜ በሐራጅ የሚሸተው የ7ኛ የፍ/ባለዕዳ የግል ቤቶች ናቸው የተባሉትን 2 ክፍል ቤቶች ሳያካትት ፍርድ ያረፈበትን ቤት ብቻ ሲሆን ገዢው የከተማው መሬት አስተዳደር በመለሰው ምላሽና እስኬች መሰረት የሚረከብ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 16,940,028 ( አስራ ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሺህ ሃያ ስምንት ብር) የትሪዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበትወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ስም c.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ⁄ዳይሮክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

 የፌዴራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-07 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 05, 2026
  • Posted at: 2026-06-05T08:08:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders