የጂንካ ማረሚያ ተቋም ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል የምግብ እህሎች፤ ቅመማ ቅመም፤ አትክልት እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጂንካ ማረሚያ ተቋም ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል የምግብ እህሎች፤ ቅመማ ቅመም፤ አትክልት እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚሁ ዘርፍ የተሰማራችሁ ተጫራቾች (ነጋዴዎች) ከዚህ በታች በወጣው ማስታወቂያ ዝርዝር መስፈርት መሠረት ቀርባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።
የተጫራቾች መስፈርት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው (ያላት)
2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር ያለውና መረጃውን ማቅረብ የሚችል
3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ
4. የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅርብ የሚችል
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለበቆሎ፣ ጤፍ፣ ፊኖ ዱቄት፤ አተር ክክ፣ ካሳባና ማገዶ እንጨት ለእያንዳንዱ 100,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ጨው፣ በርበሬ፣ ሽንኩርት፤ እርሾና እርድ ለእያንዳንዱ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በጥሬ ገንዘብ) በቅድምያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ዋጋ 50 ብር /ሃምሳ ብር/
8. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ጂንካ ማረሚያ ተቋም ቢሮ ቁጥር 4
9. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ በጨረታ ሳጥን ወስጥ የሚገባ ሲሆን በእለቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
10. የእቃው ርክክብ የሚፈፀምበት ቦታ ጂንካ ማረሚያ ተቋም
ማሳሰቢያ፤
ሀ/ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046 875 9067
የጂንካ ማረሚያ ተቀም
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Publishing entity: Jinka Correctional Facility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 50 (ሃምሳ ብር)
- Published: Jun 06, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.