በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የግልፅ ጨረታ ቁጥር 08/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ ባለ ሶስት እግር ተሸከርከሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልፅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በግልፅ ጨረታ ቁጥር 08/2018 በ09/10/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡት ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች፦

1. ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ዲጅታል ብሔራዊ መታወቅያ ያለው

2. ለጨረታ የቀረበው ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሸከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው።

3. የተሸከሪካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም።

4. በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከ29/09/2018 ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ 6 ሰአት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት ተሸከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።

5. ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

6. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው።

7. ተጫራቾች ባለ ሶስት እግር ለተሸከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት።

8. ተጫራቾች ተሸከርካሪውን ለመግዛት የሚያቀርባውን የመጫረቻ ዋጋ ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ 5% በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በዕለቱ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3፡45 ድረስ በድሬዳዋ ሙድአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

10. ጨረታው ከጠዋቱ 3፡50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ጉምሩክ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል።

11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

12. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሸከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ተሸከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል።

13. ከላይ በተራ ቁጥር 12 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሸከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ ይቀርባል።

14. የጉምሩከ ኮምሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል።

በኢትዮጵያ በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-16
  • Publishing entity: Ministry of Customs Diredawa Branch Bureau
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 06, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders