የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሙሉ ከበደ እና በፍ/ባለዕዳ መሀመድ ሰንዴው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.161424 በ10/10/2016ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.169980 በ02/03/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ ለገጂራ ቀጠና ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር የካ/194565/08 ሴሪያል 110921 በአዲሱ ካርታ ቁጥር LMK 10713283823036303 የተመዘገበ የቦታ ሰፋት 230.36 ካ/ሜ E-ካርታ የሆነ በግራ ቀኙ ወገኖች የተመዘገበ ቤዝመንት ያለው ጂ+3 የሆነውን መኖሪያ ቤት የሐራጅ መነሻ 25,296,440 (ሃያ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ ለምለም አምባ ከሚባለው ስፍራ የሚገኝ ቤትና ይዞታ በቁጥር IMK 1131132341766 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ሰፋት 176 ካ/ሜ E-ካርታ የሆነ የሐራጅ መነሻ 5,746,944 ( አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ cPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-10
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-07-10 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T08:54:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.