የቤትና ቦታ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ ከሳሽ - 1. አቶ ዮናስ ግርማይ ዉብነህ
2. አቶ መርሃዊ ለገሰ መብራህቱ
በአፈ/ተከሳሾች - 1. አቶ ተስፋአለም ዘመንፈስ ገ/ሚካኤል
2. ወ/ሪት ልዋም ዘመንፈስ ገ/ሚካኤል
3. ወ/ሮ ፍረወይኒ ዘመንፈስ ገ/ሚካኤል
4. አቶ መድሃንየ ዘመንፈስ ገ/ሚካኤል
መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር አስመልክቶ በአዲግራት ከተማ ቀበሌ 04
በሟች ወ/ሮ ፃድቃን ተካ ገ/ማርያም ስም የሚታወቅ አዋሳኙ ምስራቅ መንገድ፣ ምእራብ - ሀይሉ አድሓኖም፣ ሰሜን መንገድ፣ ደቡብ - አቶ ጥዑም በርሀ የሚያዋስነው 250 ሜ/ካሬ ያለው ቤትና ቦታ ለማስፈፀሚያ እንዲውል በዚህ ፍርድ ቤት ስለተፈለገ ከላይ የተገለፀው ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ 2,896,890.37 (ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ ስምንት መቶ ዘጠና 37/00 ብር) በጨረታ እንዲሸጥ፣ ጨረታ የሚካሄደው ቤቱና ቦታው በሚገኝበት በአዲግራት ከተማ ሲሆን ጨረታ የሚካሄድበት ቀን
02/11/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡30 ቆይቶ ከቀኑ 6፡30 ላይ ይዘጋል። የጨረታ አሸናፊ ከታወቀ ጨረታ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25% በቅድሚያ ያስይዛል። ቀሪው 75% ገንዘብ ደግሞ በ15 ቀናት ውስጥ በአንድ ላይ ገቢ ያደርጋል። የቤቱ ስመ ሀብት ለማዘዋወር የሚያስፈልግ ክፍያ በጨረታ አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል። የጨረታው ውጤት በ03/11/2018 ዓ/ም 3፡00 ሰዓት ላይ ወደ መቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል።
የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-09
- Publishing entity: Mekelle City High Court
- Published: Jun 07, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.