የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩኘ አባል የሆነው ድርጅታችን ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ለሥራ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ሠነድ

የጨረታ ቁጥር Disposal MIG-MCE 002/2018

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩኘ አባል የሆነው ድርጅታችን ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ለሥራ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1 ተጫራቾች አዲስ አበባ፣ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ከመካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ከኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቀጥሎ ባለው የኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 1ኛ ፎቅ የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

2. በጨረታው ለመሣተፍ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሆን ይችላል በጨረታ የሚሣተፈው ድርጅት ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅትና በበጀት ዓመቱ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰነድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለጨረታ ያቀረቡትን ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/CPO/ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ አንብበው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እንዲያቀርቡ ይመከራሉ።

5. ተጫራቾች አዲስ አበባ ቃሊቲ አዲሱ ተርሚናል እና አሮጌ ተርሚናል ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት 09 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ተሽከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚፈልጓቸውን የተሽከርካሪ ዓይነትና የሠሌዳ ቁጥር ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ የሚገዙበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመጥቀስ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስአት ከግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያና ሲፒኦ በስም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ። ጨረታው ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ጠዋት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል።

7. ሻጭ ድርጅት ማንኛውንም የመንግስት ዕዳ ከፍሉ ተሽከርካሪዎቹን ለመሸጥ የሚያስፈልግ ክሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት ያቀርባል፣

8. ገዥ ግለሰብ ወይም ድርጀት ለሚገዟቸው ተሽከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ እና በመንገድ ትራንስፖርት ግምትና የሽያጭ ውል ልዩነት ካለ ለአገር ውስጥ ገቢዎች ሚኒስቴር የሚከፈል ወጪ በጨረታ አሸናፊዎች ይሸፈናል

9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት/ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሽከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግና የሽያጭ ውል በመዋዋል ተሽከርካሪውን ማንሳት ሲኖርበት ተሽከርካሪውን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል።

10. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል።

11. ሻጭ ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉም ሆነ በከፊልየመስረዝ መብት አለው።

አድራሻ፡- ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ኢትዮ አገሪሴፍት ቅጥር ገቢ ውስጥ

ማሳሳቢያ፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251 91 267 9874/ 09 66 21 51 42/ 09 11 90 09 60/ +251 09 19 48 77 62 ይጠቀሙ።

ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ አና ለማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-18 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Midroc Construction Ethiopia P.L.C.
  • Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T11:38:22.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders