የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክስዮን ማህበር መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የኦሮሚያ ኀብረት ሥራ ባንክ
በድጋሚ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች ስማቸው ለተገለጻው ተበዳሪ ያበደረውን የብድር ገንዘብ በብድር ውሉ መሠረት ስላልተከፈለ ባንኩ 97/90 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መከፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆን ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበውንና ያሳገደውን ንብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪው የብድር እዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ዕለት እና አድራሻ(ቦታ) በመቅረብ በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ተጋብዟል።
|
ተራ ቁጥር |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የንብረት ዓይነት |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ |
||
|
ከተማ |
ዞን/ክ/ከተማ |
ወረዳ/ቀበሌ |
|||||||||
|
1 |
አቶ ወርቁ ለማ ሁንዴ |
አቶ ወርቁ ለማ ሁንዴ |
የጋራ መኖሪያ ቤት |
ሆራ አሪሰዲ |
ቢሾፍቱ |
ድባዩ |
ሆራ |
B/M2/B10/1ST/R10/4 |
61.86 ካ.ሜ
|
2,238,394.26 |
ሐምሌ 1 ቀን 2018ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 ሰዓት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሆራ አርሰዲ ቅርንጫፍ ውስጥ አንደኛ ፎቅ ላይ በድጋሚ ይካሄዳል። |
|
2 |
አቶ ምትኩ ፈቀደ ዋጅ |
ወ/ሮ ሲሳይ ንጉሴ |
መኖሪያ ቤት
|
ቢፍቱ
|
ድሬዳዋ |
ድሬዳዋ |
02 |
DD001026803021 |
250.11 ካ.ሜ
|
4,565,066.17 |
ሐምሌ 9 ቀን 2018ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 ሰዓት የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ቢፍቱ ቅርንጫፍ ግብ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ይካሄዳል። |
ተጫራቾች እንዲያውቋቸው
- ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ስም አሰርተው ይዘው በመቅረብ ቅርንጫፉ በሚገኝበት አድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ። ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፍቃድና የድርጅቱን ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
- ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማስታወቂያ ላይ በተገለጸ አድረሻ ይካሄዳል። ባለእዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተራ ቁጥር 1 የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሆራ አሪሰዲ ቅርንጫፍ በስ.ቁ 09 10-74 78 29/ 09 21-76 01 51 እና ለተራ ቁጥር 2 ቢፍቱ ቅርንጫፍ በስልክ ቁጥር 09 12-77 25 65/ 09 13-28 91 40 በመደወል መጎብኘት ይቻላል።
- በተራ ቁጥር 1 የተቀመጠ የጋራ መኖሪያ ቤቱን ተጫርቶ ላሸነፈ እና የብድር መስፈርቱን ለሚያሟላ እንዲሁም ተጨማሪ ዋስትና ማቅረብ ለሚችል አሸናፍ ተጫራች ባንኩ ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ እስከ 50% ብድር ያመቻቻል።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15(አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወይንም ጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
- የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫትና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙ ወደ እራሱ እንዲዛወር ያደርገል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-16 12:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Cooperative Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T12:27:41.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.