ቡሉኮ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለድርጅቱ ሠራተኞች የማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በግዥ መለያ ቁጥር BISC/NCB/Ser/12/2018
ቡሉኮ ጨርታጨርቅ አክሲዮን ማህበር ለድርጅቱ ሠራተኞች የማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
የተሽከርካሪ ብዛት |
የኩባንያው የሥራ ጊዜ (ሽፍት) |
የተሽከርካሪው የደርሶ መልስ ጊዜ |
|
1 |
ከፍተኛ አውቶብሶች (ከ60 ሰው በላይ) |
17 |
1 ሽፍት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ከቀኑ 11፡00 |
1 |
|
2 |
ከፍተኛ አውቶብሶች (ከ60 ሰው በላይ)
|
6 |
3 ሽፍት • ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት • ከቀኑ 9፡00 እስከ ምሽቱ 5፡00 ሰዓት ከምሽቱ 5፡00 እስከ ጠዋቱ 1፡00 ሰዓት |
3 |
|
3 |
ሚኒባስ መኪናዎች
|
5 |
1 ሽፍት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ከቀኑ 11፡00 |
1 |
ስለሆነም በጨረታው ላይ የሚሣተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ማሟላት አለባቸው።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ወይም የባንክ ያለገደብ ጋራንቲ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማቅረብ የሚችል።
6. የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ባሸነፉት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆኑ ለተሸነፉት ደግሞ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው ሲ.ፒ.ኦ በቡሉኮ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ወይም “Buluk Textile Share Company" ስም መሆን ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ሸገር ከተማ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ 1.3 ኪሜ ላይ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ከሰዓት በኃላ ከ7፡30 – 10፡30 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
8. ጨረታው ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች በተገኙበት 5፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0996-67-2951 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡
ሸገር ከተማ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3 ኪ.ሜ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ
የቡሉኮ ጨርታጨርቅ አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-02
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-07-02 11:10
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Buluko Textile Share Company
- Buyer address: ሸገር ከተማ፣ ፉሪ ክ/ከተማ (ከኬንትሪ ወደ ቡታጅራ መንገድ 1.3ኪ.ሜ) የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር)
- Published: Jun 08, 2026
- Posted at: 2026-06-09T07:19:31.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.