በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጌዴኦ ዞን ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ዲቪዥን ሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ለህግ ታራሚዎች የምግብ ቀለብ የሚውል እህል፣ የባልትና ውጤቶች፣ የምግብ አላቂ ዕቃዎች እና ለምግብ ማብሰያ የሚውል የማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ለህግ ታራሚዎች የምግብ ቀለብ ግዥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ ቁጥር 03/2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጌዴኦ ዞን ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ዲቪዥን ሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ለህግ ታራሚዎች የምግብ ቀለብ የሚውል እህል ፣የባልትና ውጤቶች፣ የምግብ አላቂ ዕቃዎች እና ለምግብ ማብሰያ የሚውል የማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡-
1ኛ, ነጭ ሰርገኛ ጤፍ / የተበጠረ/ 2ኛ. የተበጠረ ቦሎ 3ኛ, በማሽን የተፈጨ የስንዴ ዱቄት/ፍኖ 4ኛ. ምስር 5ኛ ያልተቆላ የባቄላ ከከ 6ኛ. ያልተቆላ አተር ክክ 7ኛ, የባልትና በርበሬ 8ኛ, ቃሪያ 9ኛ. የምግብ ጨው 10ኛ. ጥሬ የጎመን ዘር 11ኛ. ቀይ ሽንኩርት 12ኛ. የምግብ ዘይት 13ኛ. የእርሾ ካሜራ 14ኛ. እርድ 15ኛ, የዕቃ ማጠቢያ ሽቦ 16ኛ. ምጣድ 17ኛ. አከንባሎ 18ኛ ሰፌድ 19ኛ, መሳቢያ 20ኛ, ዛላ በርቤሬ 21ኛ. ነጭ ሽንኩራት 22ኛ. ነጭ ቅሜም 23. የወጥ ማጣፈጫ 24ኛ, የማገዶ እንጨት መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ጨረታ የሚካሄደው የሥራ ቋንቋ አማርኛ ስሆን በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የክፈሉና ፈቃዳችሁን ያሳደሱ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ፣በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ከመንግሥት ገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ መስክ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 /አስር ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ህጋዊ ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ የተጠቀሱ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በየሎት የተዘጋጀውን ከዲላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ቡድን ገዝተው ከሞሉ በኃላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ አሥራ አምስተኛው ቀን 5፡45 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ከታሸገ በኃላ በእለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዲላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ባይሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ወደ ጨረታ ሣጥን አስገብተው በከፈታ እለት የማይገኙ ቢሆን እንኳ ጨረታው ይከፈታል።
አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም። የጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ ጊዜ ጀምሮ የስድስት ወሩን አቅርቦት ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ አቅርበው ውል መፈጸም አለባቸው። አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው እንደተገለጸ ውል የማይፈጽሙ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/አይመለስም። የጨረታውን ዝርዝር በጨረታ አፈጻጸም መመሪያ ላይ የተገለጸ ስለሆነ በይበልጥ ተቀባይነት ያለው ለጨረታ የተዘጋጀ ሠነድ በመሆኑ ማንበብ ይኖርባቸዋል።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ: በስልክ ቁጥር 046-331-3085 / 046-331-7754 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የዲላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/ር ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Publishing entity: Dilla Correctional Facility
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jun 08, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.