የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ወይም ድርጅት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

15ኛ ዙር የንግድ/ድርጅት ቤቶች ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ/ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/09/2018

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በስሩ የሚገኙ የንግድ ድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አገ/11/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

2. ኮርፖራሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ/ድርጅት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ የኪራይ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።

4 ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ከፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚከናወን ይሆናል።

6. ተጫራቾች የንግድ ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09 10-48-59-48 / 09 22-49-18-85 ወይም 09 22-98-76-33 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት website www.fhc.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ. PO Box 299

ፋክስ ቁጥር፡-011-554-6045/ 011-552-4646

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-06-29 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Housing Corporation
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T08:35:21.000Z
  • Buyer website: https://www.fhc.gov.et

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders