የቦታ ስፋቱ 440 ካሬ ሜትር የሆነ መኖሪያ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ጋሻ ፋይናንስ አነስተኛ ብድር አክሲዮን ማህበር እና በፍርድ ባለዕዳ አቶ መኮንን ተፈራ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ የፍርድ አፈፃፀም ባለዕዳ ንብረት የሆነው የመኖሪያ ቤት በምስራቅ አላሚሼት ሚሂርካ በምዕራብ-መስፈን የሺ በሰሜን መንገድ በደቡብ-በሙላት ዘውዴ ይዞታ ወሰን በአቶ መኮንን ተፈራ ይዞታ የተመዘገበው በካርታ ቁጥር 129 በ 22/03/2012 ዓ.ም የተመዘገበውና በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ኪሎሌ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው የቦታ ስፋቱ 440 m2 የሆነው የመኖሪያ ቤት የመነሻ ዋጋው በብር 1,252,491.22 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሃያ ሁለት ሳንቲም) ተገምቶ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ አዟል።

በመሆኑም መግዛት የሚፈልግ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በግልጽ ጨረታው ላይ እንዲሳተፍ እየተጋበዘ ጨረታው በአየር ላይ ከሚቆይበት ጊዜ ጀምሮ ለሽያጭ የቀረበውን ንብረት መግዛት የሚፈልግ ተጫራች ካለ ጨረታው በ 21/10/2018 ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ የሚካሄድ ሲሆን ይኸው የመጀመሪያ ዙር የሐራጅ ጨረታ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ላይ ኮሚቴው ባለበት እንዲከናወንና የጨረታው አሸናፊ የሆነው ሰው የጨረታውን ዋጋ 25% በCPO (ሲ.ፒ.ኦ) በቁጥር እንዲያስይዝ የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-06-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-28 12:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T08:58:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders