በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለድርጅት 1512 ካ.ሜ እና ለመኖሪያ 160 ካ.ሜ ጠቅላላ ስፋታቸው 1672 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

2018 ዓ.ም 5ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ለድርጅት 1512 ካ.ሜ እና ለመኖሪያ 160ካ.ሜ ጠቅላላ ስፋታቸው 1672 ካሬ ሜትር የሆኑ ለመኖሪያና ድርጅት አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚህም መሰፈረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

የጨረታውን ሰነድ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

1. ተጫራቶች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specifection/ መሰረት መሆን ይኖርበታል። ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ከፍያ ማዘዣ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ20 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

3. ተጫራቾች የቅድመ ክፍያ ከጠቅላላው ብር ላይ 30% መከፈል የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

4. የጨረታ አሸናፊዎችን ለመለየት የሚከተሉትን የማወዳደሪያ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ይሆናል፡-

ሀ) ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ 80%

ለ) የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን 20% የሚያዝ ይሆናል

5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ 02/10/2018 እስከ 15/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ15/10/2018 ዓ.ም 11:00 ሰዓት ይሆናል።

7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16/10/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዮን/ እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ በስም ዝርዝር ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።

10. የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥሮች 0913 501 899 / 033 554 0255 / 0913 259 920 ወይንም Gmail address Ke.ketemaaglglot@gmail.com መጠየቅ ይችላሉ።

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-06-23 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kemise City Administration Urban and Infrastructure Development Office
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T09:17:28.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders